ቆየት ያሉ የኢትዮጵያ የንግድና የአገልግሎት ምልክቶችን የሚያሳይ አውደ ርዕይ በዛሬው እለት ተከፍቷል፡፡
አውደ ርዕዩ ለሶስት ቀናት የሚቆይ ሲሆን አዘጋጁ ደግሞ በሲዊዲን ሀገር ነዋሪው አቶ ኤፍሬም በየነ ናቸው።
ለሶስተኛ ዓመት በተከታታይ የተዘጋጀው አውደ ርዕይ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ፣ የአንበሳ መድሃኒት ፣ የዳግማዊ የአፄ ሚኒሊክ መኪና ታርጋን ጨምሮ 28 ብራንዶችን ይዟል።
በኢትዮጵያ የነበሩ ቀደምት ምልክቶቾ በየአመቱ ለተመልካቹ የሚያቀርበው ብራንዲንግ እና ኮሙኒኬሽን አውደርይ ላይ ከአጼ ሚኒሊክ ዘመን አንስቶ እስከ ዛሬ ድረስ ኢትዮጵያን የሚገልጹ ምልክቶች ቀርበዋል።
ከቀረቡት ምልክቶች መካከል አጼ ሚኒሊክ ይጠቀሙበት የነበረው የመኪናቸው ታርጋ፣ የሀይማኖት ተቋማት ምልክቶች፣ የሆቴል ቤት ምልክቶች እና ሌሎችም ቀርበዋል።
በኢትዮጵያ የመንግስት ለውጥ በመጣ ቁጥር ኢትዮጵያን የሚገልጹ ምልክቶች በሌላ እየተተኩ ይገኛል።
የመንግስት መስሪያ ቤቶች ከተቋማቸው ጋር የማይጣጣም ምልክት አየተጠቀሙ እንደሆነም ነው የገለጹት።
የብራዲግ እና ኮሚኒኬሽን አውደርዕይ አዘጋጅ የሆነው አቶ ኤፍሬም በየነ ተቋማት አውደርዩን ቢጎበኙት ብዙ እንደሚማሩበትና እንደሚያተርፉበትም ገልጸዋል፡፡
በሔኖክ ወ/ገብርኤል
መስከረም 03 ቀን 2016 ዓ.ም
