በሃማስ ሮኬቶች እየተናጠች የምትገኘዉ ሀገረ እስራኤል የጋዛ ክልል በወታሮቿ እንዲወረር ትዕዛዝ ሰጥታለች፡፡
የሀገሪቱ መካለካያ ሚኒስትር ዮኣቭ ጋላት የጋዛን ሰርጥ በቀለበት ዉስጥ ለማስገባት ትእዛዝ ተሰጥቷል፡፡
የምግብ ነዳጅና ሌሎች መሰረታዊ አገልግሎቶችም ወደ ጋዛ እንዳይደርሱ ዕገዳ ተጥሏል፡፡
እስራኤል ባጋዛ እየወሰደች ባለችዉ የአየር ጥቃት በጃባሊያ ስደተኞች መጠለያ የሚገኙ ዜጎች መገደላቸዉን አልጄዚራ ዘግቧል፡፡
ይሁን እንጅ ሃማስ እየወሰደ ባለዉ የሮኬት ጥቃቶቸ በእስራኤል ከተሞች ከፍተኛ ፍንዳታዎች እየተሰሙ ነዉ ተብሏል፡፡
በጋዛ የሞቱት ሰዎች ቁጥር 5መቶ 10 ሲደርስ 2 ሺህ 7 መቶ 50 ደግሞ ተጎድተዋል፡፡
በእስራኤል በኩል ደግሞ የሟቾች ቁጥር 8 መቶ ደርሷል ነዉ የተባለዉ፡፡
በአባቱ መረቀ
መስከረም 28 ቀን 2016 ዓ.ም
