በአውደ ርዕዩ ላይ ኔዘርላንድን ጨምሮ ከ17 አለምአቀፋዊ ሀገራት በተውጣጡ ተሳታፊዎች በተገኙበት በሚሊኒየም አዳራሽ ተጀምሯል ።
የንግድ ትርዒት አዘጋጅ በሆነው ፕራና ኢቨንትስ የተዘጋጀው ይህ አውደርእይ ለሶስት ቀናት እንደሚቆይ ተገልጿል ።
50 በመቶ የተሳታፊ ኩባንያዎች ብዛት እና የማሳያ ቦታ ሽፋን እድገትን ያሳያል የተባለለት ይህ በአውድርዕይ ከ100 በላይ አለምአቀፍ የዘርፉ መሪዎችና ስመጥር የሃገር ውስጥ ኩባንያዎች ይሳተፋሉ ተብሏል ።
መሰል አውደርእይዎች አለምአቀፋዊ የገበያ ሰንሰለቶች ላይ የኢንቨስትመንት እድሎችን ለማስተዋወቅ ፣የገበያ ትስስርን ለመፍጠር አቅም እንዳለው ተነስቷል ።
በተጨማሪም የእውቀትና የቴክኖሎጂ ሽግግርን ለማምጣት አውደርእይው በእንስሳት እና በግብናው ዘርፍ ታዋቂ የሆነችውን ኔዘርላንድን እያሳተፈ እንደሆነ ተገልጿል ።
ኢትዮጵያ ከፍተኛ የእንስሳት ሃብት ባለቤት ብትሆንም በዘርፉ ላይ ያላት ምርታማነት እና የነፍስ ወከፍ ፍጆታ ዝቅተኛ ነው ተብሏል ።
በመሳይ ገ/መድህን
ጥቅምት 16 ቀን 2016 ዓ.ም
