ዴቪድ ካሜሮን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው ተሾሙ፡፡

የቀድሞው የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስትር የነበሩት ዴቪድ ካሜሮን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው ተሹመዋል፡፡

ዴቪድ ካሜሩን እንግሊዝን ከፈረንጆቹ 2010 እስከ 2016 ድረስ በጠቅላይ ሚኒስትርነት ማገልገላቸው ይታወሳል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው የተሾሙት ዴቪድ ካሜሩን፣ ከስድስት አመታት በኋላ በከፍተኛ የመንግስት የሃላፊነት ቦታ ወደ ስልጣን ተመልሰዋል።
በቅርቡ ወደ ስልጣኑ የመጡት ጠቅላይ ሚኒስትር ሪሺ ሱናክ የስልጣን ሽግሽግ እያደረጉ ይገኛሉ፡፡

የስልጣን ሽግሽግ ከተደረገባቸው ቦታዎች መካከል አንደኛው የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ይገኝበታል፡፡
በስራቸው ትሁት እንደሆኑ የሚነገርላቸው ካሜሮን እንግሊዝ ከቅርብ አመታት ወዲህ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲዋ ጥያቄ እየተነሳበት ይገኛል፡፡

ዴቪድ ካሜሮን ይህንንና ሌሎችም የውጭ ፖሊሲዎች ያሻሽላሉ ተብሎ እምነት ተጥሎባቸዋል፡፡

በሔኖክ ወ/ገብርኤል

ህዳር 03 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *