በዓለማችን የሚገደሉ ሴቶች ቁጥር ካለፉት 20 ዓመታት ወዲህ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ መጨመሩን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) አስታወቀ ።
እንደ ፈረንጁቹ አቆጣጠር ባላፈው ዓመት 89 ሺህ ዐዋቂ እና አዳጊ ሴቶች ሆነ ተብሎ ግድያ ተፈጽሞባቸዋል ።
ይህንንም በተመድ የሴቶች ጉዳይ፤ እንዲሁም የአደንዛዥ እጽ እና ወንጀል ጉዳዮች ጽ/ቤቶች ዐስታውቀዋል ።
ከአጠቃላይ ሴቶች ላይ ከደረሰው ግድያ ከግማሽ በላይ ማለትም 55 በመቶ የተፈጸመው በቤተሰብ አባላት አለያም በአጋሮች ነው ብሏል ዘገባው ።
አብዛኞቹ በአዋቂ እና አዳጊ ሴቶች ላይ ግድያዎች የተፈጸሙት አፍሪቃ ውስጥ ሲሆን ቁጥሩም 20 ሺህ ይጠጋል ተብሏል ። በሁለተኛ ደረጃ ላይ የእስያ አኅጉር ሰፍሯል ።
ህዳር 14 ቀን 2016 ዓ.ም
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
