ፕ/ር ሙላቱ ለማ የዓመቱ ምርጥ ፕሮፌሰር በመሆን ተመርጠዋል፡፡

ፕ/ር ሙላቱ ለማ በጆርጂያ ሳቫና ግዛት ዩኒቨርሲቲ የሂሳብ መምህር ናቸው፡፡

ኢትዮጵያዊው ፕ/ር ሙላቱ ለማ የ2023 ምርጥ ፕሮፌሰር በሚል ነው የተመረጡት።

ፕ/ር ሙላቱ ለማ በዘርፍ የተመረጡት በዓለም አቀፉ ከፍተኛ ባለሙያዎች ማህበር መሆኑን የአሜሪካ ኤምባሲ አስታውቋል።

ማህበሩ በዓለም አቀፍ ደረጃ በሙያዊ ስኬት፣ በአካዳሚክ ውጤት፣ በአመራር ችሎታ፣ በመስኩ ረጅም ጊዜ በማገልገል እና ለማህበረሰብ ባደረጉት አስተዋፅዖ በመመርኮዝ ለባለሙያዎች እውቅና እና ክብር ይሰጣል።

ከ30 ዓመታት በላይ የሂሳብ ትምህርትን ያስተማሩት፣ፕ/ር ሙላቱ ለማ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በሂሳብ የመጀመሪያ እና ሁለተኛ ዲግሪያቸውን አግኝተዋል።

በኦሃዮ ከኬንት ግዛት ዩኒቨርሲቲ በሂሳብ የዶክትሬት ዲግሪያቸውን ያገኙ ሲሆን ፥ ለ28 ዓመታትም በሳቫና ግዛት ዩኒቨርሲቲ አስተምረዋል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ታህሳስ 01 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *