ግሎባል ባንክ ኢትዮጰያ ከግብር በፊት 836 ሚሊዮን ብር በላይ ትርፍ ማግኘቱን አስታወቀ።

የቀደሞው ደበብ ግሎባል ባንክ ያሁኑ ግሎባል ባንክ ኢትዮጰያ የባለ አክሲዮኖች ማህበር በተጠናቀቀው በጀት አመት ከ 3 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ በመሰበሰብ ከታክስ እና የእርጅና ቅናሽ (Depreciation) በፊት ከ836 ሚሊዮን በላይ ማትረፉን ገልጿል።

ባንኩ የበጀት አመቱን አፈፃፀም አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ የሰጠ ሲሆን ከፍተኛ ትርፍ አስመዝግቢያለሁ ብሏል።

በዚህም መሰረት

  • ባንኩ ያስመዘገበው የትርፍ ምጣኔ ከባለፈው አመት ጋር ሲነፃፀር 88 በመቶ ብልጫ እንዳለው ሲገልፅ የትርፍ ምጣኔው ከሌሎች ባንኮች ጋር ሲነፃፀር ከፍተኛ መሆኑን ገልጿል።
  • ለባለ አክሰዮኖቹ የሚከፍለው የትርፍ ድርሻ በቀደመው የበጀት አመት ከነበረው 18.1 በመቶ ወደ 29.2 በመቶ ማደጉን ሲገልፅ እድገቱ 23 በመቶ መሆኑን ጠቅሷል።
  • የባንኩ ጠቅላላ ሀብት 19 ቢሊዮን የደረሰ ሲሆን ይህም ካለፈው ዓመት የ34 በመቶ ብልጫ እንዳለው ተገልጿል።
  • የባንኩ ተቀማጭ ገንዘብ 14.3 ቢሊዮን መድረሱ ሲገለፅ ከቀደመው የበጀት አመት 30 በመቶ በማደግ ፥ ውጪ ያለው ብድርም 13.7 ቢሊዮን ብር መድረሱን አሳውቋል።
  • ፋይናንስ ነክ ባልሆኑ ጉዳዮችም ባንኩ እድገት ማስመዝገቡን ሲገልፅ የባንኩ አጠቃላይ ደንበኞች ብዛት 1.2 ሚሊዮን መድረሱን ሲገልፅ ካቻምና ከነበረበት የ75 በመቶ እድገት አሳይቷል። የቅርንጫፎቹን ብዛትም 152 አድርሻለሁ ብሏል።
  • ባንኩ ማህበራዊ ሃላፊነቱን ለመወጣት 30 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ ማድረጉ ገልጿል። የተከፈለ ካፒታሉን 2.1 ቢሊዮን ብር ማድረሱ ሲገልፅ የባለ አክሲዮኖቹ ብዛትም 20 ሺህ መደረሱን አሳውቋል።

የቀደሞው ደበብ ግሎባል ባንክ ያአሁኑ ግሎባል ባንክ ኢትዮጰያ የባለ አክሲዮኖች አመታዊ ጠቅላላ ጉባዔውን ታህሳስ 06/2016 ዓ.ም በአዲስ አበባ ሚሊኒየሞ አዳራሽ እንደሚያካሂድ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ አሳውቋል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ታህሳስ 04 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *