ፐርፐዝ ብላክ በግብርናው ዘርፍ የፈጠራ ስራ ውድድር ሽልማት ሊያካሄድ መሆኑም ታውቋል፡፡
የፈጠራ ስራ ሽልማት ውድድሩ በግብርናው ዘርፍ የልምድ እንደዚሁም የእውቀት ልውውጥ ለማደረግ ያለመ እንደሆነ እና አነስተኛ ማሳ ያላቸውን ገበሬዎች ምርታማነታቸውን ለማሳደግ ያለመ ነው ተብሏል።
ውድድሩ የፈጠራ ስራ ሀሳቦች ወደ ተግባር ለመለወጥ ትልቅ አጋጣሚ መሆኑንም ተነግሯል።
ውድድሩ በየሳምንቱ የሚካሄድ ሲሆን ለአንድ ወር ይቆያልም ተብሏል።
በግብርናው ዘርፍ የተሻለ ሀሳብ ያላቸው ተወዳዳሪዎች ውጤታማ እንዲሆኑ ከፐርፐዝ ብላክ የቴክኒክ ድጋፍ እንደሚደረግላቸውም ሰምተናል፡፡
ከዚሁ ጋር በተያያዘም ፐርፐዝ ብላክ ከባድ የተባሉ ችግሮች እየገጠሙትም ቀለብ ከገበሬው በመረከብ ለተጠቃሚው እያቀረበ እንደሚገኝ ተናግሯል።
ድርጅቱ ተሸከርካሪዎቹ ለስራ ሲንቀሳቀሱ በተለያዩ ጊዜያት ጥቃት እየደረሰባቸው እንደሚገኝም በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ተናግሯል።
በሔኖክ ወ/ገብርኤል
ታህሳስ 15 ቀን 2016 ዓ.ም
