ኢትዮጵያ በሰብአዊ ነፃነት ከነበራት ደረጃ ዝቅ ማለቷን የአለም አቀፉ የሰብዓዊ ነፃነት መረጃ ተቋም ሂውማን ፍሪደም ኢንዴክስ አስታወቀ።

ከሰሃራ በታች ካሉት 45 ሀገራት መካከል ኢትዮጵያ በዜጎች ነፃነት 39ኛ ደረጃ ላይ መቀመጧን ሪፖርቱ አ ይፋ አድርጓል፡፡

በአለም አቀፋዊ እይታ ስናየው ደግሞ ኢትዮጵያ በአለም አቀፍ ደረጃ ከ1 መቶ65 ሀገራት 1 መቶ 48ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች።

በሶማሊያ እና በሱዳን ከሰሃራ በታች ያሉ የአፍሪካ ጎረቤት ሀገራትም ከዝርዝሩ ግርጌ ላይ ተቀምጠዋል።

በአለም አቀፍ ደረጃም የመን እና ሶሪያ የመጨረሻውን ደረጃ መያዛቸው በአገሮቹ ያለውን አስከፊ ሁኔታ ያሳያል ይላል ሪፖርቱ።

መረጃ ጠቋሚው የግል እና ኢኮኖሚያዊ ነጻነትን ለመለካት 86 የተለያዩ አመልካቾችን ተጠቅሟል።

እነዚህ አመላካቾች በዓለም አቀፍ ደረጃና ደንብ መሰረት የህግ የበላይነትን፣ ደኅንነትን፣ እንቅስቃሴን፣ ሃይማኖትን፣ ማህበርን፣ ስብሰባን፣ የሲቪል ማኅበራትን ነጻነት በመለኪያነት በመጠቀም የወጣ ነዉ ተብሏል፡፡

በተጨማሪም መግለጫን፣ መረጃን፣ ግንኙነትን፣ የሕግ ሥርዓትን፣ የንብረት መብትን፣ የድምጽ ገንዘብን፣ የመገበያያ ነፃነትን ጨምሮ የተለያዩ ዘርፎችን ያካተቱ ናቸው።

በሀመረ ፍሬዉ
ታህሳስ 16 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *