አሜሪካ ማዕከላዊ ኮማንድ በሰጠው መግለጫ በሁቲዎች በ10 ሰዓታት ውስጥ የተተኮሱትን አስራ ሁለት በአንድ አቅጣጫ የሚያጠቁ ድሮኖች፣ ሶስት ፀረ-መርከብ ባለስቲክ ሚሳኤሎችን መቶ መጣሏን አስታዉቋል፡፡
በተጨማሪም ጦሩ ሁለት የምድር አጥቂ ክሩይዝ ሚሳኤሎችን በደቡብ ቀይ ባህር መምታቱን ገልጧል።
የማዐከላዊው ኮማንድ በዓማፂያኑ የየመን ሁቲዮች በተሰነዘረው ጥቃት በአካባቢው ላይ በነበሩ መርከቦች ምንም አይነት ጉዳት አልደረሰም ማለቱን ሲጂ ቲ ኤን ዘግቧል፡፡
የየመን ሁቲዎች በቀይ ባህር ሰሜናዊ ክፍል በምትገኘው ኢላት በተባለችው የእስራኤል ከተማ ለደረሰው ጥቃት ሃላፊነቱን ወስደዋል።
በልዑል ወልዴ
ታህሳስ 17 ቀን 2016 ዓ.ም
