ኢትዮጵያ በሊዝ የወደብ ባለቤት መሆኗ ተሰማ፡፡ By ethiofmAdminJanuary 1, 2024January 1, 2024የሀገር ውስጥ ዜና ኢትዮጵያ የቀይ ባሕር በር ለማግኘት እና ለማልማት የሚያስችላትን ስምምነት ከሶማሊ ላንድ ጋር ፈፅማለች ተባለ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና የሶማሊ ላንድ ፕሬዚዳንት ሙሴ ባሂ ሁሉን አካታች የሆነውን የጋራ መግባቢያ ሰነድ ተፈራርመዋል። በዚሁ መሠረት ለብዙ ዘመናት ወደብ አልባ ሆና የቆየችው ሀገራችን ከሶማሊ ላንድ ጋር ባደረገችው ስምምነት በሊዝ የወደብ ባለቤት መሆን ችላለች ተብሏል፡፡