ሴራሊዮን የመንግስት ግልበጣ ለማድረግ ሞክረዋል ያለቻቸዉን 27 ወታደሮች ላይ ክስ መስርታለች፡፡

የሴራሊዮን መከላከያ ቢሮ እንዳለዉ ባለፈዉ ህዳር ወር ላይ በወታደራዊ ግምጃቤቶች እና በአንዳንድ እስርቤቶች ሰብሮ በመግባት የመንግስት ግልበጣ ለማድረግ ተሞክሮ ነበር ብሏል፡፡

በዚህም የሴራሊዮን ፍርድ ቤት መፈንቅለ መንግስቱን ለማድረግ ሙከራ አድርገዋል ባላቸዉ 27 ወታደሮች ላይ ክስ መስርቷል፡፡

ወታደሮቹ በጭካኔ፣ ጉዳትን ማስቆም ባለመቻል፣ ግድያ፣ ጠላትን በመርዳት፣ ከጠላት ጋር በመገናኘት በሚሉ እና በሌሎች ጉዳዮች ተጠርጥረዉ ክስ እንደተመሰረተባቸዉም ተገልጿል፡፡

ባለፈዉ ህዳር ወር የታጠቁ ሃይሎች ወደ ወታደራዊ ግምጃቤቶች እና እስርቤቶች በመግባት ወደ 2ሺህ የሚሆኑ እስረኞች እንዲያመልጡ አድርገዋል ነዉ የተባለዉ፡፡

ባለስልጣናቱም ይህን ጉዳይ መንግስትን ለመጣል የተደረገ ሙከራ ነዉ በማለት ገልጸዉታል፡፡

ባለፈዉ ሳምንት ከዚህ ጉዳይ ጋር በተያያዘ የቀድሞዉ ፕሬዝዳንት ኤርነስት ኮሮማ በአገር ክህደት ወንጀል የተከሰሱ ሲሆን፤ እሳቸዉ ግን በሁኔታዉ ምንም ዓይነት ተሳትፎ እንደሌላቸዉ ተናግረዋል፡፡

በ27ቱ ወታደሮች ላይ የተከፈተዉ ክስም በትናንትናዉ ዕለት በፍርድ ቤት መታየት የጀመረ ሲሆን፤ ለዕሮብ ዕለትም ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቶበታል፡፡

መንግስትን ለመገልበጥ ሙከራ የተደረገዉ ፕሬዝዳንት ጁሊየስ ማዳ በድጋሚ ከተመረጡ ከ5 ወራት በኋላ ነዉ፡፡

የፕሬዝዳንቱ በድጋሚ መመረጥ በተቃዋሚ ቡድኖች እና በዓለም ዓቀፍ ደረጃ ግልጽነት ይጎድለዋል በሚል ተቀባይነትን አላገኘም ነበር፡፡

በእስከዳር ግርማ
ታህሳስ 30 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *