በቀይ ባህር ወደ እስራኤል የሚሄዱ መርከቦች ላይ የሚፈፅሙት ጥቃት ለጋዛ የሚደርሰውን ድጋፍ ‘አይከለክልም’ ሲሉ ሁቲዎች አስታወቁ።

በየመን እና አከባቢው የሚንቀሳቀሱት ሁቲዎች የጋዛን ጦርነት ተከትሎ በቀይ ባህር ወደ እስራኤል የሚሄዱ መርከቦችን ማጥቃት እንደሚቀጥሉ መናገራቸውን ሲዘገብ ቆይቷል።

የሁቲዎች እንቅስቃሴን ለመግታት እንዲሁም የአከባቢውን ሰላማዊ እንቅስቃሴ ለማረጋገጥ በሚል አሜሪካና እንግሊዝ በትንትናው እለት በየመን ላይ ጥቃት መጀመራቸውን አስታውቀዋል።

የሁቲ ቡድን ቃል አቀባይ የሆኑት መሐመድ አብዱልሰላም በበኩላቸው በየመን ላይ ለተፈጸመው ጥቃት ምንም አይነት ምክንያት እንደሌለ አረጋግጠናል ሲሉ ገልፀዋል ።

በአረብም ሆነ በቀይ ባህር ላይ ለአለም አቀፍ የባህር ጉዞ ላይ የተጋረጠ ምንም አይነት ስጋት አለመኖሩ ሀገራቱ ለጥቃት መነሻ የላቸው ሲሉም ጠቁመዋል።

ቃል አቀባዩ አክለውም አሜሪካ እና እንግሊዝ  “የመን ፍልስጤም እና ጋዛን ከመደገፍ ትቆጠባለች” በሚል እሳቤ የፈፀሙት ጥቃት “የተሳሳተ” ነው ሲሉም አስታውቀዋል ።

ቡድናቸው ሲሰነዝር የነበረው ጥቃት ” ኢላማው የእስራኤል መርከቦችን እንዲሁም በቁጥጥር ስር ወደዋሉ የፍልስጤም ወደቦች በሚያመሩት ላይ ተፅዕኖ ለማሳደረ ነበረ፤ ይህም ይቀጥላል” ሲሉ በኤክስ( ቲውተር) ላይ ፅፈዋል።

ሆኖም የሚሰነዝሩት ጥቃት እስራኤልን ለማስቆም የሚረዳ እንጂ ወደ ጋዛ የሚደርሱ ድጋፎችን የሚከለክል አለመሆኑ ሊታወቅ ይገባል ሲሉ ባጋሩት ፅሁፍ ጠቁመዋል

ሀመረ ፍሬው
ጥር 03 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *