የsu-30 ተዋጊ ጀቶች እና የስትራቴጂክ ሰው አልባ ተዋጊ አውሮፕላኖች (ድሮኖች) የመጀመሪያ ዙር ርክክብ በዛሬው እለት መከናወኑን የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት በማህበራዊ ትስስር ገጹ ባወጣው መረጃ አስታውቋል፡፡
ርክክቡ ላይ የጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ፣ “በአለማችን ላይ ተመራጭ የሆኑትን የsu-30 እና የስትራቴጂክ ሰው አልባ አውሮፕላን ባለቤት መሆናችን በሀገራችን ላይ ሊቃጡ የሚሞከሩ ጥቃቶችን ለማክሸፍ ወሳኝ ናቸው” ብለዋል።
የ5ኛ ትውልድ አካል የሆኑት ዘመናዊ ተዋጊ አውሮፕላኖችና የስትራቴጂክ ስው አልባ አውሮፕላኖች አየር ሀይሉን የማዘመን አንዱ አካል መሆናቸውንም ጠቁመዋል።
ጥር 07 ቀን 2016 ዓ.ም
