200 ሰዎች ከህልፈተ ሕይወት በኋላ የአይን ብሌናቸውን ሊለግሱ ቃል ገብተዋል ተባለ፡፡

114 የሚሆኑ ሰዎች ደግሞ የዓይን ብሌናቸውን መለገሳቸው ተገልጿል
ባለፉት ስድስት ወራት ውስጥ 200 የሚሆኑ በጎ ፈቃደኛ ሰዎች ከህልፈተ ሕይወት በኋላ የዓይን ብሌናቸውን ለመለገስ ቃል መግባታቸውን የኢትዮጵያ ደም እና ህብረ ህዋስ ባንክ አስታውቋል፡፡

ከ10 ዓመት በፊት በተጠና ጥናት 300 ሺህ የሚሆኑ ሰዎች ዓይናቸው ላይ በደረሰ ጠባሳ ምክንያት፣የአይን ብሌን ንቅለ ተከላ እንደሚያስፈልጋቸው የኢትዮጵያ ደም እና ህብረ ህዋስ ባንክ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ሃብታሙ ታዬ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል።

በአሁኑ ወቅት በጥናቱ ከተገለጸው የዓይን ብሌን ንቅለ ተከላ የሚያስፈልጋቸው ቁጥር ሊጨምር ይችላል ሲሉ ገልጸዋል፡፡
እንደ ሀገር አንድ የዓይን ብሌን ባንክ ብቻ መኖሩን እና በአዲስ አበባ የዓይን ብሌን እንደሚሰበስብ ገልጸው፤ በክልል በጎንደር፣ በጅማ፣ በመቀሌ እና በሃዋሳ የዓይን ብሌን ንቅለ ተከላ እንደሚከናወን ነግረውናል፡፡

በ2016 ግማሽ ዓመት 114 የዓይን ብሌን መሰብሰብ መቻሉን የገለጹ ሲሆን፤ ባሳለፍነው ዓመት 190 የሚሆኑ ሰዎች ቃል መግባታቸውን አስታውሰዋል፡፡

ከዓይን ብሌን ፈላጊዎች ብዛት ጋር ሲነጻጻር ግን አሁንም የዓይን ብሌን ለጋሾች ቁጥር ዝቅተኛ መሆኑንም ጨምረው ገልጸዋል፡፡

በእሌኒ ግዛቸው

ጥር 08 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *