የአዲስ አበባ እሳትና አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን በዓለ ጥምቀተ በባህሩ ቦታና ታቦታቱ ከመንበራቸዉ ሲወጡም ሆነ ሲመለሱ በነበሩ እንቅስቃሴዎች ሁሉ ምንም ዓይነት አደጋ እንዳላጋጠማቸው ለጣቢያች ገለፁ።
የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ለጣቢችእንደተናገሩት ከበዓላቱ ቀናት አስቀድሞ ከሀይማኖት አባቶች ፣ ከበዓሉ አስተባባሪዎችና ከባለድርሻ አካላት ጋር በተለያዩ መድረኮች ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራን በመስራቱና ህብረተሰቡም ከኮሚሽን መ/ቤቱ የተላለፉ የጥንቃቄ መልዕክቶችን ተግባራዊ በማድረጉ በዓሉ በሰላም ተከብሯል ብለዋል።
ሆኖም በበዓሉ ዋዜማ በከተራ ዕለት በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ ሁለት ራስ ደስታ ሆስፒታል ፊት ለፊት እንደዚሁም በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 በግተራ እየተባለ በሚጠራዉ አካባቢ በአጋጠሙ ሁለት የእሳት አደጋዎች ሰባት የንግድ ሱቆች ላይ ጉዳት ደርሷል።
የኮሚሽኑ የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች በሁለቱም ቦታዎች ያጋጠሙት የእሳት አደጋዎች ተዛምተዉ የከፋ ጉዳት ሳያደርሱ መቆጣጠር ችለዋል።
በአደጋዉ በሁለት የእሳት አደጋ ሰራተኞች ላይ ቀላል ጉዳት ደርሷል።
በቀጣይ ቀናት በሚኖሩም እንቅስቃሴዎች ሁሉ ማህብረሰቡ ጥንቃቄዉን አጠናክሮ መቀጠል ይኖርበታል።
ልኡል ወልዴ
ጥር 13 ቀን 2016 ዓ.ም
