የኮንፌደሬሽኑ ፕሬዚዳንት አቶ ካሳሁን ፎሎ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት “የዝቅተኛ ደመወዝ ወለል እንዲቀመጥና ሰራተኛው ላይ የተጫነው ግብር እንዲቀነስ ያስገቡትን ጥያቄ ከፍትህ ሚኒስትር መልስ ካላገኙ ጥያቄውን ወደ ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንደሚወስዱትም ተናግረዋል።
አቶ ካሳሁን ፎሎ ” የመጨረሻ አማራጫችን ጥያቄያችንን በድጋሚ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ማቅረብ ነው” ብለዋል ።
አቶ ካሳሁንደሞዝ ተከፋይ ሰራተኛው ኑሮ ውድነቱ እሱ ከሚያገኘው በላይ እንደሆነ አንስተው የኑሮ ውድነቱ ቢጠነክርም የደሞዝ ተከፋይ ሰራተኛው ገቢ እንዳላደገ አንስተዋል።
በዚህም ለሰራተኞች የዝቅተኛ ደመወዝ ወለል እንዲቀመጥና ሰራተኛው ላይ የተጫነው ግብር እንዲቀነስ ጥያቄያቸው መልስ እስከሚያገኝ ድረስ መጠየቅ እንደማያቆሙም ገልፀዋል።
ማህበሩ የደሞዝ ተከፋይ ሰራተኛውን የግብር ቅነሳን በተመለከተ ለፍትህ ሚኒስትር ጥያቄ አቅርቦ እስካሁን ምላሽ እንዳላገኙ መዘገባችን ይታወሳል።
በለአለም አሰፋ
የካቲት 14 ቀን 2016 ዓ.ም
