በኢትዮጵያ የመሬት ጥያቄ ምላሽ ሊያገኝ አልቻለም ተባለ።

በኢትዮጵያ ከ50 ዓመት በኃላም የመሬት ጥያቄ ምላሽ ሊያገኝ አልቻለም ሲል የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ፓርቲ /ኢህአፓ/ አስታወቀ፡፡

ኢህአፓ እና መሰል ድርጅቶች ሲታገሉለት የነበሩት የመሬት ላራሹ እና ህዝባዊ መንግስት የይቋቋም ጥያቄ ዛሬም ምላሽ አላገኘም መባሉን ኢትዮ ኤፍ ኤም ሰምቷል፡፡

ከዛሬ 50 ዓመት በፊት የተጀመረው የመሬት ላራሹ ንቅናቄ የገበሬውን የመሬት ባለቤትነት ለማረጋገጥ የተደረገ ንቅናቄ ነበር፡፡

የመሬት ላራሹን ጥያቄ መልስ ይሠጣል የተባለለትን አዋጅ ደርግ የካቲት 25 1967 ቢያወጣው

መሬትን መሸጥም ሆነ መለወጥን በመከልከሉ ለጥያቄ ትክክለኛ መልስ መመለስ ያልቻለ አዋጅ ነው ሲሉ የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ፓርቲ ኢህአፓ ዋና ሊቀመንበር ፕሮፌሰር ዝናቡ ለኢትዮ ኤፍኤም ተናግረዋል፡፡

እናም ይህ አዋጅ ዛሬም ድረስ በህገ-መንግስቱ መቀመጡን በማንሳት 50 ዓመት ሙሉ ይህን ጉዳይ መሻሻል ሲገባው ትኩረት ሊሰጠው አልተፈለገም ነው ያሉት፡፡

መሬት የፖለቲካ መጫወቻ ካርድ መሆኑንም ጠቁመው በዚህ ምክንያ ት ገበሬው ተጠቃሚ ሳይሆን 50 ዓመት አልፎታል ብለውናል፡፡

አኢሃፓ ህገ-መንግስቱ እንዲቀየር ከሚጠይቅባቸው ጉዳዮች አንዱ የመሬት ጥያቄ ነው ።

ህዝብ የመሬት ባለቤት መሆን ነበርበት ይሁን እንጂ የመንግስት አካላት በህገወጥ መንገድ ሲመዘብሩት መመልከት የተለመደ ነው ሲሉም የኢሃፓው ሊቀመንበር ከሰዋል።

በአቤል ደጀኔ

የካቲት 21 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *