የካፒታል ገበያውን ሊያጋጥሙ የሚችሉ የወንጀል ተግባራትን የህግ ማዕቀፍ እንዲኖረው ና ገበያውን በቴክኖሎጂ ለመደገፍ የሚያስችል ስምምነት ተደረገ፡፡

የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን የባለስልጣኑን ተዓማኒነት ይጨምራል፤ የህግ ስርዓቱን ያጠናክራል እንዲሁም ስራውን በቴክኖሎጂ ለማፋጠን ያስችለዋል የተባለውን የመግባቢያ ስምምነት በዛሬው እልት ከባለድርሻ አካላት ጋር ተፈራርሟል።

የባለስልጣኑ ዳይሬክተር ዶር ብሩክ ታዬ እንዳሉት፣ ባለስልጣኑ ወደ ስራ ሲገባ ሊያጋጥሙ የሚችሉ የወንጀልም ሆነ የማጭበርበር ስራዎችን የህግ ማዕቀፍ እንዲኖረው የሚያስችል ስምምነት እንደሆነ ተናግረዋል።

የፍትህ ሚኒስትሩ ዶር ጌዲዮን ዲሞጢዎስ በበኩላቸው በገበያው ላይ ያሉ የህግ ጥሰቶችን ለመቆጣጠር የሚያስችል ስምምነት እንደሆነ ገልጸዋል።

በመድርኩ የተገኙት የፌድራል ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሸነር፣ ስምምነቱ ከካፒታል ገበያ ውጭ የአክሲዮን ሽያጭ በሚያደርጉት ላይ ሰፋ ያለ ቁጥጥር ለማድረግ እንደሚያስችል ተናግረዋል።

በሌላ በኩል ባለስልጣኑ የካፒታል ገበያውን በቴክኖሎጂ ለመደገፍ የሚያስችል ስምምነት ከኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ከአርቴፊሻል ኢንተለጀስ እንዲሁም ከብሄራዊ መታወቂያ ጋር አድርጓል

በዚህም ገበያውን በቴክኖሎጂ የታገዘ ማድረግ ለባለስልጣኑ ትልቅ አቅም እንደሚፈጥር ያነሱት ዶር ብሩክ ታዬ፣ ባለስልጣኑ ያደረገው ስምምነትም ይሀንን ታሳቢ ያደረገ ነው ሲሉ አንስተዋል።

ባለስልጣኑ ከባለድርሻ አካላት ጋር ያደረገው ስምምነት ካፒታል ገበያው ለረጅም ጊዜ እንዲቆይ እንዲሁም ነፃ የሆነ ስራ ለመስራት የሚያስችል ስምምነት እንደሆነም ተገልጿል።

በለዓለም አሰፋ

የካቲት 21 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *