የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ እርዳታ ሰጭዎች ትናንት እንዳስታወቁት በሰሜን ኢትዮጵያ በድርቅ ሳቢያ የተከሰተውን እና የከፋ የረሃብ ሁኔታን ለማስታገስ 17 ሚሊየን ዶላር ለቀዋል።
የመንግስታቱ ድርጅት የሰብአዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ አማካኝነት ከማዕከላዊ የአደጋ ጊዜ ምላሽ ፈንድ የተለቀቀው ይህ ገንዘብ በኤልኒኖ ምክንያት የተከሰተው አዲስ ድርቅ በአፋር፣ አማራ እና ትግራይ ክልሎች ላይ እያደረሰ ያለው ጉዳት አሳሳቢ መሆኑ ነዉ ተብሏል።
“አዲሱ ድርቅ እየተባባሰ በመምጣቱ ከሐምሌ እስከ መስከረም ባለው የዝናብ ወቅት በመላው ኢትዮጵያ ከ10 ሚሊዮን በላይ ሰዎች የምግብ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል ተብሎ እንደሚጠበቅ ኦቻ አስታዉቋል ።
የካቲት 22 ቀን 2016 ዓ.ም
