በአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ላይ ምርመራ እንዲደረግ ውሳኔ ተላልፏል::

ፕሬዚዳንቷና ዋና ጸሐፊው ተጠያቂ ሊሆኑ ይችላሉ ተብሏል፡፡

ከአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የዳይሬክተሮች ቦርድ ዕውቅናና ውሳኔ ውጪ፣ በምክር ቤቱ ላይ የተለያዩ ሕገወጥ ተግባራት ተፈጽመዋል በማለት፣ የኦዲት ምርመራ እንዲደረግ የምክር ቤቱ ዳሬክተሮች ቦርድ ውሳኔውን አሳልፏል፡፡

ቦርዱ ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ በምክር ቤቱ ተፈጽመዋል ያላቸውን የተለያዩ ሕገወጥ ተግባር የሚያጣራ ኮሚቴ ማቋቋሙም ታውቋል፡፡

በምክር ቤቱ ላይ ተፈጽመዋል ከተባሉት ግድፈቶች መካከል፣ በተለይ የምክር ቤቱ ዋና ጸሐፊ ከቦርዱ ዕውቅናና የምክር ቤቱ የአሠራር ፖሊሲ ውጪ፣ በርካታ የውጭ ጉዞዎችን በማድረግ፣ በመቶ ሺዎች የሚገመት የውጭ ምንዛሪ ወጪ ማድረጋቸውንና፣ ከ15 ሺሕ በላይ የሚሆነው የምክር ቤቱ አባላት ሀብት እንዲባክን ማድረጋቸው ተነግሯል፡፡

ኃላፊዎቹ ሕገወጥ የሠራተኞች ቅጥር ማካሄድ፣ ሠራተኞች ማሰናበት፣ የደረጃ ዕድገት መስጠት፣ ከቦርዱ ዕውቅና ውጪ የተፈጸሙ የብልሹ አሠራር ሒደቶች መሆናቸውን የቦርዱ ውሳኔ ያብራራል፡፡

የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ወ/ሮ መሰንበት ሸንቁጤና ዋና ጸሐፊው አቶ ሺበሺ ቤተ ማርያም፣ ተፈጠሩ የተባሉትን ችግሮች በተመለከተ ቦርዱ እንዲያጣራ ውሳኔ ማሳለፉን አረጋግጠው፣ ነገር ግን የቀረበባቸው አቤቱታና ቅሬታ ትክክል አለመሆኑንና፣ ምክር ቤቱ ሕግና ሥርዓቱን ጠብቆ እየሠራ ስለመሆኑ፣ በበቂ ማስረጃ ማሳየት እንደሚቻል ተናግረዋል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
የካቲት 25 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *