አንድ እና ሁለት ሰው ስለሞተ በክልሉ የጸጥታ ችግር አጋጥሟል ማለት አይቻልም” ሲሉ የጋምቤላ ክልል የጸጥታ ሀላፊ ተናግረዋል።
የክልሉ የፀጥታ ዘርፍ ዋና ሃላፊ አቶ ቹል ኩል ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደገለጹት ጋምቤላ ክልል ያጋጠሙ የጸጥታ ችግሮችን መቆጣጠሩን እና የፀጥታ ስጋት እንደሌለበት ገልጸዋል።
ክልሉ በአኝዋክ እና ኑዌር ጎሳዎች መካከል በሚፈጠር ግጭት የጸጥታ ችግሮች እንደሚያጋጠሙ የሚናገሩት የጸጥታ ሃላፊው አሁን ላይ ግን ያለምንም ስጋት ማህበረሰቡ ስራውን እሰራ ነው ሲሉ ተናግረዋል
አንድ እና ሁለት ሰው ስለሞት በክልሉ የጸጥታ ችግር አጋጥሟል ማለት አይቻልም የሚሉት ሃላፊው በሁለቱ ጎሳዎች ያሉትን ችግሮች በውይይት ለመፍታት እየተሞከረ እነደሆነ ገልጸዋል፡፡
በክልሉ በትራንሰፖርት ላይ የሚደረስ መስተጓጓል እና ያልተፈቱ ግጭቶች እንዳለ የሚያመኑት ሃላፊው ታዲያ ይህንን ተንተርሶ በጋምቤላ የጸጥታ ችግር አለ ብሎ መናገር ልክ አደለም ሲሉም አክለዋል፡፡
ሃላፊው ይህንን ይበሉ እንጂ ኢሰመኮ በቅርቡ ባወጣው መግለጫ በጋምቤላ ክልል በተፈጠሩ ግጭቶች የብዙ ሰዎች ህይወት እንደተቀጠፉ ጣቢያችን መዘገቡ የሚታወስ ነዉ።
በለአለም አሰፋ
የካቲት 27 ቀን 2016 ዓ.ም
