የቀድሞ ተዋጊዎችን የማቋቋም ስራ እየተሰራ መሆኑን የተሃድሶ ኮምሽን አስታወቀ፡፡

በመጀመሪያ ዙር 75 ሺህ የቀድሞ ተዋጊዎችን መልሶ የማቋቋም ስራ እየሰራ መሆኑን የተሃድሶ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡
በመጀመሪያው ዙር የሚቋቋሙት 75 ሺህ የቀድሞ ተዋጊዎች ከትግራይ ክልል ናቸው፡፡

ለሶስት ዓመታት የሚቆየው የተሃድሶ ኮሚሽን እስካሁን ባለው አንድ ዓመት ውስጥ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እያከናወነ መቆየቱን የኮሚሽኑ የፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሻንቆ ደሳለኝ ለኢትዮ ኤፍኤም ተናግረዋል፡፡

በሚቀጥሉት ሶስት ዓመታት በአገር ደረጃ በሚተገበረው ትጥቅ የማስፈታትና መልሶ ማቋቋም ፕሮግራም 371,971 የቀድሞ ተዋጊዎች ተጠቃሚ እንደሚሆኑ የሚጠበቅ ሲሆን ፕሮግራሙን ለማሳካት በጠቅላላው ከ760 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር በላይ ያስፈልጋል።

ከዚህ ዉስጥ 15% ማለትም 115 ሚሊዮን በላይ የአሜሪካን ዶላር በመንግስት የሚሸፈን ሲሆን ቀሪዉን የአገር ዉስጥና በዉጭ የልማት አጋሮች እንደሚሸፈን ሀላፊው ተናግረዋል፡፡

ሰኔ 2016 ላይ የመጀመሪያ ዙር የመልሶ ማቋቋም ስራውን በትግራይ ለማስጀመር ከ60 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ እንደሚደረግም ከ ኮምሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ከመንግስት የሚጠበቀው 15 በመቶ የሆነው ድርሻ በቀጣይ በጀት ዓመት ገቢ እንደሚሆን ይጠበቃል ተብሏል፡፡

አገራዊ የዘላቂ ሰላም ግንባታ አካል የሆነዉን ተልዕኮ ለማሳካት ኮሚሽኑ በሰባት ክልሎች 371,971 የሚሆኑ የቀድሞ ተዋጊዎችን ለመመለስ እየሰራ ሲሆን ብዙ የቀድሞ ተዋጊ ያለበት የትግራይ ክልል 75 ሺህ ተዋጊዎች በሰኔ ወር የመልሶ ማቋቋም ስራ ይስራል ብለዋል፡፡

ከትግራይ በመቀጠል በኦሮሚያ፣ቤንሻንጉል፣በአፋር እና በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ተግባራዊ የሚደረግ ሲሆን በአማራ ክልል ያለው የፀጥታ ሁኔታ ለመልሶ ማቋቋም አመቺ ባለመሆኑ በጊዜያዊነት ያለመያዙን ተናግረዋል፡፡

በሃገሪቱ ትጥቅ የማስፈታትና መልሶ ማቋቋም በደርግ ውድቀት ማግስት እና ከኢትዮ ኤርትራ ጦርነት በኃላ መደረጉ ይታወሳል፡፡

በአቤል ደጀኔ
የካቲት 27 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *