ዛሬ መጋቢት 2 ቀን 2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 2:30 ላይ በአዲስ አበባ ስድስት ኪሎ ዩኒቨርስቲ ቢዝነስና ኢኮኖሚ ፉክልቲ በተማሪዎች ማደሪያ ህንጻ ላይ የተነሳዉ የእሳት አደጋ ሙሉ በሙሉ በቁጥጥር ስር ዉሏል።
የእሳትና የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የህዝብ ግኑኘነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ የእሳት አደጋዉን ለመቆጣጠር አራት የአደጋ መቆጣጠር ተሽከርካሪና ሁለት አምቡላንስ ከ 32 የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ጋር መሠማራታቸውን ገልጸዋል።
አቶ ንጋቱ የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች በአደረጉት ርብርብ እሳቱን በፍጥነት መቆጣጠር መቻሉን አስታውቀዋል።
የእሳት አደጋዉ እንደ እንደ አጋጠመ በህንጻዉ የነበሩ ተማሪዎች ፈጥነዉ ከህንጻዉ ለቀዉ የወጡ ሲሆን ዘግይተዉ የነበሩ አራት ተማሪዎች በእሳት አደጋ ሰራተኞች ምንም ጉዳት ሳይደርስባቸዉ ከህንጻዉ ወጥተዋል ተብሏል።
በአደጋዉ በሰዉ ላይ ምንም ጉዳት አልደረሰም።
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
መጋት 02 ቀን 2016 ዓ.ም
