የዉሃ እና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ዶ/ር ኢንጅነር ሃብታሙ ኢተፋ ባለፉት 18 ወራት ለጎረቤት አገራት ከተሸጠ የሃይል አቅርቦት ከ 1 ቢሊየን ዶላር በላይ ገቢ መገኘቱን ገልጸዋል፡፡
ለሱዳን፣ ግብጽ እና ኬንያ በተሳካ ሁኔታ ሃይል ማቅረብ ችለናል ያሉት ሚኒስትሩ ፤ ይህም በኬንያ እና በኢትዮጵያ መሃል ያለዉን ግንኙነት ያጠናከረ ነዉ ብለዋል፡፡
ከኬንያ ጋር ባለዉ ግንኙነትም ወደ ደቡብ አፍሪካም የሃይል ሽያጭ ማድረግ እንድንችል የሚረዳን ነዉ ሲሉ ገልጸዋል፡፡
ሚኒስትሩ የኢትዮጵያ የሃይል አቅርቦት 93በመቶ የሚሆነዉ ከዉሃ የሚመነጭ መሆኑን ገልጸዉ፤ አገራችን ወደ ደቡብ ሱዳን የምታደርገዉን የሃይል ሽያጭ ለማስፋት ማሰቧንም ተናግረዋል፡፡
በአገር ደረጃ የተለያዩ ለዉጦች መኖራቸዉን ገልጸዉ፤ ባለፉት 6 ወራት 4.5 ሚሊየን ደንበኞች ከሃይል ስርዓቱ ጋር መገናኘታቸዉን ገልጸዋል፡፡
አሁንም ህዝቡ ተበታትኖ በመኖሩ ምክንያት ሃይልን በሚፈለገዉ ልክ ማቅረብ አልተቻለም ያሉት ሚኒስትሩ ፤በአሁኑ ሰዓት በአገሪቱ የሚገኘዉ 52 በመቶ ህዝብ ብቻ የሃይል አቅርቦት እንደሚያገኝ ገልጸዋል፡፡
በ2022 ኢትዮጵያ ከደቡብ ሱዳን ጋር ለ3 ዓመት የሚቆይ የ100 ሜጋዋት የሃይል ሽያጭ ስምምነት መፈራረሟ የሚታወስ ነዉ፡፡
ይህም የደቡብ ሱዳንን የሃይል ፍላጎት በማሟላት ለኢትዮጵያም ገቢ የሚያስገኝ ሲሆን፤ በጊዜ ሂደትም ወደ 400 ሜጋዋት ከፍ ለማድረግ መታሰቡም ተገልጿል፡፡
በእስከዳር ግርማ
መጋቢት 11 ቀን 2016 ዓ.ም
