በምዕራብ አርሲ ሀገረ ስብከት በዶዶላ የደብረ ቅዱሳን ቅዱስ ገብረ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን 2 አገልጋዮች ከነሙሉ ቤተሰቦቻቸው ጋር ለጊዜው ” ማንነታቸው አልታወቀም ” በተባሉ አካላት መገደላቸው ተነግሯል።
የቴሌቪዥን ጣቢያው ፤ ግድያው የተፈፀመው ትናንት መጋቢት 16 ቀን 2016 ዓ.ም ከምሽቱ 3:00 ገደማ መሆኑን የአካባቢው ምዕመናን እንደነገሩት ገልጿል።

በተፈጸመው በዚህ ግድያ የደብረ ቅዱሳን ቅዱስ ገብረ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን አገልጋይ የሆኑት አንድ መሪጌታና ዲያቆንን ጨምሮ 5 የቤተሰብ አባሎቻቸው በጥይት ተደብድበው መገደላቸው ተገልጿል።
የቴሌቪዥን ጣቢያው ፥ በዶዶላ ከተማ ጥቅምት 12 ቀን 2012 ዓ.ም በርካታ ኦርቶዶክሳውያን መገደላቸውን አስታውሷል።
መጋቢት 17 ቀን 2016 ዓ.ም
