በመላ ሀገሪቱ ኃይል መቋረጡ ተገለፀ By Ethio AdminMarch 28, 2024የሀገር ውስጥ ዜና ዛሬ ከቀኑ 9 ሠዓት 46 ጀምሮ ከባህርዳርና አካባቢው በስተቀር በመላው ኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ኃይል ሙሉ በሙሉ መቋረጡን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታወቀ፡፡ ሲስተም ላይ በገጠመ ችግር ኃይል የተቋረጠ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን÷ ለጊዜው የችግሩን ምክንያት ለማወቅ ጥረት እየተደረገ ነው ተብሏል። የተቋረጠውን ኤሌክትሪክ መልሶ የማገናኘት ሥራ የተጀመረ መሆኑም ተመላክቷል፡፡