የሲቪክ ማህበረሰብ ድርጅቶች ከባለሀብቶች ማግኘት የሚገባቸው ገቢ እያገኙ አለመሆኑ ተገለፀ፡፡

ባለሀብቶች ለሲቪክ ማህበረሰብ ድርጅቶች እርዳታ ባደረጉ ቁጥር በዓመት ግብራቸው ላይ 15 በመቶ ይቀንስላቸዋል የሚለው መመሪያ ተግባራዊ መሆን አለመቻሉ ተነግሯል፡፡

የቪዥን ኢትዮጵያ ኮንግረስ ፎር ዲሞክራሲ ዋና ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ታደለ ደርሰህ ከጣብያችን ኢትዮ ኤፍ ኤም ጋር በነበራቸው ቆይታ ይህ መመሪያ ተግበራዊ መሆን ያልቻለው ባለሀብቶች ባላቸው ስጋት ምክንያት ነው ብለውናል፡፡

በሲቪክ ማህበረሰብ ድርጅቶች መተዳደሪያ ደንብ ላይ በግልፅ ቢቀመጥም አብዛኛው ባለሀብት በተለይም ከሰብዓዊ መብት እና ከዲሞክራሲ መብት ድርጅቶች ጋር መስራት ያስጠይቀናል ብለው ስለሚሰጉ ምንም ድጋፍ ተገኝቶ አያውቅም ብለዋል፡፡

መንግስት በሰብዓዊ እና ዲሚክራሲ መብት ላይ የሚሰሩ ድርጅቶችን የመጠበቅ ሀላፊነት ቢኖርበትም ይህንን ማድረግ አልተቻለም ሲሉም። ከሰዋል፡፡

በተለይም ከቅርብ ግዜያት ወዲህ በርካታ ረጂ ተቋማት ድጋፋቸውን የመተው አዛማሚያ እያሳዩ መሆኑ ሲቪክ ማህበረሰብ ድርጅቶቹ ችግር ውስጥ እንዲቆዮ አድርጓቸዋል ሲሉ ለጣብያችን ተናግረዋል፡፡

የሲቪክ ማህበረሰብ ድርጅቶች በከፍተኛ የገንዘብ እጥረት ተዳርገዋል የሚሉት አቶ ታደለ በርካቶቹ የቤት ኪራይ መክፈል እንኳን እየከበዳቸው ይገኛሉ ብለዋል፡፡

በመሆኑም ሲቪክ ማህበረሰብ ድርጅቶች ለህብረተሰቡ እንደሚሰሩ ከግምት በማስገባት መንግስት ድጋፍ ሊያደርግላቸው እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡

በአቤል ደጀኔ
መጋቢት 26 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *