በኦሮምያ ክልል በስምንት ጣበያዎች እስካሁን ድረስ ምርጫ ማከናወን አልተቻለም ተባለ።

በክልሉ ከ178 የምርጫ ክልሎች ውስጥ በ8ቱ ጣበያዎች ምርጫ እስካሁን ማከናወን አልተቻለም ተብሏል።

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከእንባ ጠባቂ ተቋምና ከኦሮምያ ምርጫ ጽ/ቤት ጋር በጋራ በመሆን በክልሉ ከሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ባደረጉት ውይይት ነው ይህ የተገለጸው።

ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በክልሉ በመንቀሳቀስ ላይ የሚገኙ ከ 25 በላይ የፖለቲካ ፓርቲዎችን በማወያየት 19 ፓርቲዎችን ያካተተ የጋራ ምክር ቤት መመስሩቱ ገልጿል።

ከጸጥታ ችግር በመቀጠል ከዋናው ቦርድ የሚሰጠው ድጋፍ አናሳ በመሆኑ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ በሚጠበቀው ልክ በክልሉ ሁሉም አካባቢ እንዳይንቀሳቀስ አድርጎታል ተብሏል።

የአስፈፃሚ አካላት ቸልተኝነት፣ የፀጥታ ችግር፣ የበጀት ችግር፣ የሰው ኃይል ዕጥረት ምርጫው እንዳይካሄድ ያደረጉ ምክንያቶች ናቸው ተብሏል

በክልሉ ያሉት የዴሞክራሲ ተቋማት የተለያዩ አማራጮች በመጠቀምና ከክልሉ መዋቅር ጋር በቅርበት መሥራት ህዝብ በመንግሥት ላይ ያለውን ዕምነት ማሳደግ እንደሚገባቸው ተገልጿል።

ምርጫ በሚደረግባቸው አካባቢዎች በነበረው የጸጥታ ችግር ምክንያት እስካሁን በስምንት ምርጫ ክልሎች ምርጫ ማከናወን እንዳልተቻለ ተገልጻል፡

የፀጥታ ችግር፣ የበጀት ችግር፣ የሰው ኃይል ዕጥረትና ከዋናው ቦርድ የሚሰጠው ድጋፍ አናሳ በመሆኑ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ በሚጠበቀው ልክ በክልሉ ሁሉም አካባቢ እንዳይንቀሳቀስ አድርጎታል ተብሏል፡፡

ሔኖክ ወ/ገብርኤል
የሚያዝያ 21 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *