ፑቲን ቻይና ገብተዋል፡፡

የሩስያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ለሁለት ቀናት ጉብኝት ቻይና መግባታቸው ታውቋል፡፡

ለአምስተኛ ጊዜ የፕሬዝዳንትነት ስልጣን የተረከቡት ፑቲን ከቻይናው ፕሬዝዳንት ሺጂንፒንግ ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ለመነጋገር ነው ቻይና የገቡት፡፡

የዩክሬን ጉዳይ እና የኒዩክሌር ሃይል ልማት ፑቲን በቤጂንግ ቆይታቸው ከሚመክሩባቸው አበይት ጉዳዮች መካከል ይገኙበታል።

በቻይና ጉብኝት ከማድረጋቸው በፊት ከቻይና የዜና አገልግሎት ሺንዋ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ሩሲያ ለንግግር ክፍት መሆኗን እና ሁለት አመት ያስቆጠረው ግጭት በሰላም እንዲፈታ እንደምትፈልግ ገልጸዋል።

ፑቲን እንደገለጹት በፕሬዝደንት ሺ አማካኝነት ባለፈው ወር ይፋ የሆነው የቻይና እቅድ ከግጭቱ ጀርባ ያሉ ጉዳዮችን ከግምት ያስገባ ነው።

“ቻይና የዩክሬይንን ቀውስ ለመፍታት ባላት አቀራረብ ላይ አዎንታዊ እይታ አለን” ብለዋል ፑቲን።
ፑቲን ወደ ቻይና ያቀኑት የሁለቱን ሀገራት ግኑኝነት የተመለከተ ነው ቢባልም የዩክሬን ጦርነት በሰላም ለመቋጨት ስምምነት እንዲደረግ መንገድ ለመጥረግ ያለመ መሆኑም ተነግራል።

ቭላድሚር ፑቲን በቻይና እና ሩስያ መካከል ዲፕሎማሲያዊ ግኑኝነት የተጀመረበት 75ኛ ዓመት እንደሚያከብሩም ነው የተገለጸው፡፡

ባለፉት 75 ዓመታት የሲኖ-ሩስያ ግኑኝነት በከባድ ግዜያት እየጠነከረ እና ተለዋዋጭ አለምአቀፋዊ ሁኔታዎችን ተቋቁሞ፤ አሁን ለሃያላን እና ጎረቤት ሀገራት ሞዴል እየሆነ ይገኛል ተብሏል፡፡
የቻይናው መሪ ሺጂምፒንግ እና ፑቲን በስልጣን ዘመናቸው ከ40 በላይ ግዜ እንደተገናቹ ስፑትኒክ ዘግቧል፡፡

ሔኖክ ወ/ገብርኤል

ግንቦት 7 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *