በድሬደዋ በትራፊክ አደጋ የ11 ሰዎች ሕይወት አለፈ፡፡

በድሬዳዋ አሥተዳደር ጀሎ በሊና ቀበሌ ቢርካ አካባቢ ሌሊት 6፡30 ገደማ በደረሰ የትራፊክ አደጋ ነው የ11 ሰዎች ሕይወት ማለፉ የተገለጸው፡፡

አደጋው የደረሰው ከድሬዳዋ ወደ ሐረር ሰው አሳፍሮ ሲጓዝ የነበረ በተለምዶ “ዶልፊን” የሚባለው ሕዝብ ማመላለሻ በተቃራኒ መስመር ይጓዝ ከነበረ በተለምዶ “ሲኖትራክ” ተብሎ ከሚጠራው የደረቅ ጭነት ተሸከርካሪ ጋር በመጋጨታቸው መሆኑ ተገልጿል፡፡

ከሟቾች በተጨማሪም በ10 ሰዎች ላይ የአካል ጉዳት መድረሱን ድሬዳዋ አሥተዳደር ፖሊስ መረጃ አመላክቷል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ሐምሌ 09 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *