ከደረጃ በታች በሚያመርቱ የፕላስቲክ ፋብሪካዎች ላይ ርምጃ መውሰዱን የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን አስታውቋል፡፡

ከደረጃ በታች የፌስታል ምርት ሲያመርቱ ከተገኙ ድርጅቶች መካከልም÷ ኤል.ኤች ማኑፋክቸሪንግ ኃ/የተ/የግ/ማኅበር፣ ኤ.ኤች ስማርት ፕላስቲክ ማምረቻ፣ ኢለኒ ፕላስቲክ ፋብሪካ፣ ሪም ፕላስቲክ ኃ/የተ/የግ/ማኅበር፣ ኤስ. ኤስ. ፕላስቲክ ፋብሪካ፣ ወይንሸት፣ ሳራና ጓደኞቻቸው ፕላስቲክ መልሶ መጠቀም ሽርክና ማኅበር፣ አግማስ ማኑፋክቸሪንግ እና ዘቢባ ፕላስቲክ ማምረቻ እንደሚገኙበት ተገልጿል፡፡

በደረቅ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ በወጣው አዋጅ ቁጥር 513/1999 መሰረትም 0 ነጥብ 03 ሚሊ ሜትር እና ከ0 ነጥብ 03 ሚሊ ሜትር በታች የሆኑ ከአፈር ጋር መዋሃድ የማይችሉ የፕላስቲክ ምርቶችን ማምረትም ሆነ ወደ ሀገር ውስጥ ማስገባት የተከለከለ መሆኑን ያስታወሰው በባለስልጣኑ ÷ የተወሰደው ርምጃም ይህን መነሻ ያደረገ ነው ብሏል፡፡

በቀጣይም ከደረጃ በታች በሚያመርቱ የፕላስቲክ ማምረቻ ድርጅቶች ላይ የተጠናከረ ርምጃ እንደሚወሰድ ባለስልጣኑ ለኢትዮ ኤፍ ኤም በላከው መረጃ አረጋግጧል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዎያን

ሐምሌ 09 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *