ፕሮፌሽናል የቦክስ ሻምፒዮና በኢትዮጵያ ሊካሄድ ነው።

ፕሮፌሽናል የቦክስ ሻምፒዮና በኢትዮጵያ ሲካሄድ እንደ በአፍሪካ አህጉርም ለመጀመሪያ ጊዜ ነው፡፡

በአፍሪካ ቦክስ ኮንፌዴሬሽን ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ፕሬዚዳንት ሆነው የተመረጡት ኢትዮጵያዊዉ አቶ ኢያሱ ወሰን በመሆናቸው ምክንያት፣ የአፍሪካ ቦክስ ኮንፌዴሬሽን ዋና ጽ/ቤት ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ አዲስ አበባ ላይ ይከፈታል።

የጽሕፈት ቤቱን መከፈት ምክንያት በማድረግም በአፍሪካ ለመጀመሪያ ጊዜ ዓለም አቀፍ ፕሮፌሽናል ቦክስ ሻምፒዮና ” Africa Unite” በሚል መሪ ሃሳብ ነሀሴ 10፣ 2016ዓ.ም አለምአቀፍ የሻምፒዮን ምሽት እንደሚካሄድ ተገልጿል።

የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ወ/ሮ ሸዊት ሻንካ: የአፍሪካ ቦክስ ኮንፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አቶ እያሱ ወሰን፣ የዓለምአቀፉ ቦክስ አሶሴሽን ጽ/ቤ ኃላፊ ሚስተር ክርስቶፈር ሮበርትስ በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ ተገኝተው ነበር፡፡

ዓለም አቀፍ ፕሮፌሽናል የቦክስ ሻምፒዮናው በስምንት የተለያዩ የኪሎ ምድቦች የሚካሄድ ሲሆን በሴቶች በ60 ኪ.ግ ሚሊየን ጨፎ ከኢትዮጵያ እና ሀድጅላ ከሊፍ ከአልጀሪያ ፤በ54 ኪ.ግ ውዳድ በርታል ከሞሮኮ እና ሳራ ሀግሂግሃት ጆ ከሴራሊዮን እንዲሁም በ75 ኪ.ግ ፓትሪሺያ ምባታ ከናይጄሪያ እና ራዲ አዶንሲንዳ ግራማኒ ከሞዛምቢክ የሚፋለሙ ይሆናል፡፡

በወንዶች በ92 ኪ.ግ ፒተር አቡቲ ከኬኒያ እና አሎሬ አድማስ ከናይጄሪያ ፤ በ75 ኪ.ግ ያሲኔ ኢሎረዝ ከሞሮኮ እና ቲያንጎ ሙታንጋ ከሞዛምቢክ ፤ በ60 ኪ.ግ አቡበከር ሴፈን ከኢትዮጵያ እና ራሺድ ኦማሪ ከሶማሌያ ፤ በ80 ኪ.ግ ፒታ ካቤጂ ከዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ እና የሱፍ ቻንጋላዊ ከታንዛኒያ ፤ በ51 ኪ.ግ ፓትሪክ ችንየምባ ከዛምቢያ እና ዴቪድ ፒና ከኬፕቨርድ በውድድሩ እንደሚፋለሙ ከወጣው መርኃ ግብር መረዳት ተችሏል።

በጋዲሳ መገርሳ

ሐምሌ 12 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *