በ2016 በጀት ዓመት በጎረቤት ሀገራት እና በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል መካከል የተደረጉት የኃይል ግዢ ስምምነቶች 113ሚሊየን ዶላር የዉጭ ምንዛሪ ገቢ ማግኘቷን የነዳጅና ኢነርጂ ባለሥልጣን አስታውቋል፡፡
በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል እና በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የቀረቡ ከብሄራዊ ግሪድ ጋር የተያያዘ የኤሌክትሪክ ታሪፍ በባለስልጣኑ ተገምግሞ ለሚንስትሮች ምክር ቤት ቀርቦ እንዲፀድቅ መደረጉን የባለስልጣኑ የኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር በቀለች ኩማ ለኢትዮ ኤፍ ተናግረዋል።
ከጎረቤት ሀገሮች ኬንያ እና ታንዛኒያ ጋር የተደረጉ የኃይል ግዢ ስምምነቶች ለባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ ቀርቦ፣ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል እና በኬንያ ኃይል አቅራቢ ድርጅት ጋር የተደረገ የኃይል ግዥ ስምምነት ተገምግሞ ጸድቆ ኃይል ወደ ኬንያ እየተላከ ይገኛል ብለውናል ።
በታንዛኒያ ኃይል አቅራቢ እና በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል መካከል የተደረገ የኃይል ግዥ ስምምነት ግምገማም በሂደት ላይ እንደሚገኝ ገልፀዋል።
ሀመረ ፍሬው
ሐምሌ 15 ቀን 2016 ዓ.ም
