በጋዛ ከተማ በሚገኙ ሁለት ትምህርት ቤቶች ላይ ባደረሰችው ጥቃት በስፍራው ተጠልለው ከሚገኙ ፍልስጤማውያን 30 የሚሆኑት መሞታቸው ነው የተገለጸው።
በዚህ ሳምንት በትምህርት ቤቶች ላይ ከደረሱ ጥቃቶች መካከል ከፍተኛው መሆኑ ተገልጿል።
ቅዳሜ ዕለት በጋዛ በሚገኙ የሃማማ እና አል-ሁዳ ትምህርት ቤቶች ላይ በደረሰው የአየር ጥቃት 17 ፍልስጤማውያን ሲገደሉ ብዙዎች መቁሰላቸው ተዘግቧል።
ሐሙስ ዕለት በተመሳሳይ በጋዛ በሚገኝ ሌላ ትምህርት ቤት ላይ በደረሰ የአየር ጥቃት 15 ፍልስጤማውያን ተገድለዋል።
የእስራኤል መከላከያ ሃይል ከጥቅምት 7 ጀምሮ የአሸባሪዎች መደበቂያ ናቸው በሚል 1መቶ52 ትምህርት ቤቶች ላይ የአየር ድብደባ አድርሷል።
እስካሁን በጦርነቱ 39ሺህ5መቶ83 ፍልስጤማውያን ተገድለዋል።
አልጄዚራ
በእስከዳር ግርማ
ሐምሌ 29 ቀን 2016 ዓ.ም
