በተጠናቀቀው በጀት አመት በከተማዋ ባሉ አስራ አንዱም ክፍለ ከተሞች ላይ በህገወጥ መልኩ ከተለጠፉት ማስታወቂያዎች 4 መቶ 79 ሺ 2 መቶ 24 የሚሆኑት ላይ እርምጃ መወሰዱን አስታውቋል፡፡
የባለስልጣን ምስሪያ ቤቱ የኮምኒኬሽን ዳይሬክተር ምስራች ግርማ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት ከዚህ ቀደም ድርጊቱን ፈፅሞ የተገኘ አካል የሚቀጣው 50 ብር የነበረ ቢሆንም አዲስ በተሻሻለው ደንብ ግን 2000 ብር ያስቀጣዋል ብለዋል፡፡
ህገወጥ የሆኑ ማስታወቂያዎች በብዛት የሚለጠፋት እና የሚበተኑት ደንብ አስከባሪዎች በማይኖሩበት እና ጨለማን ተገን በማድረግ በመሆኑ ስራችን ላይ እንቅፋት ሆኖብናል ሲሉም ተናግረዋል።
ህገ ወጥ ማስታወቂያውን የሚለጥፈው አካል የሚያስቀምጠው አድራሻ የተሳሳተ በመሆኑ ሰዎቹን ለማግኘት አስቸጋሪ እንደሚሆን ጠቅሰዋል፡፡
እንደዚህ አይነት ድርጊቶች መንግስት ማግኘት ያለበትን ገቢ እንደሚያሳጣ እና የአካባቢ ገፅታን እንደሚያበላሽ አንስተዋል፡፡
ማህበረሰቡም በድብቅ ማስታወቂያዎችን የሚያሰራጩ አካላትን በሚያይበት ጊዜ ለደንብ ማስከበር ባለስልጣን ወይም በ9995 በነፃ ስልክ መስመር ላይ በመደወል ህገወጥ ስራዎችን በማጋለጥ የበኩሉን አስተዋፅኦ ማበርከት አለበት ሲሉ ተናግረዋል።
ሐመረ ፍሬው
ሐምሌ 29 ቀን 2016 ዓ.ም
