ስደተኞች ቤተሰቦች የተገኘችው የአሜሪካ ምክትል ፕሬዝደንት ካማላ ሀሪስ በትናንትናው እለት የዲሞክራት ፕሬዝደንታዊ እጩ መሆናቸው ይፋ ሆኗል።
ሀሪሰ ይፋዊ የዲሞክራት ፓርቲ ፕሬዜደንታዊ እጩ ለመሆን ከተወካዮች በቂ ድምጽ ማግኘታቸውን አሶሼትድ ፕሬስ ዘግቧል።
ሀሪስ እጩ ለመሆን ከ4000 ተወካዮች ውስጥ የ1976ዎቹ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው የነበረ ሲሆን ከተጠበቀው በላይ አግኝተው እጩ መሆናቸው ተገልጿል።
የሀሪስ እጩነት ይፋ የሆነው የዲሞክራት ናሽናል ኮንቬንሽን ተወካዮች በኦለንላይ አማካኝነት ያደረጉት የአምስት ዙር ምርጫ በትናንትናው እለት ከተጠናቀቀ ካደረጉ በኋላ ነው።
የዲሞክራት ፓርቲ ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው 99 በመቶ የሚሆኑት ተወካዮች ድምጻቸው ለሀሪስ ሰጥተዋል።
ሐምሌ 30 ቀን 2016 ዓ.ም
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
