ከፈረንጆቹ ነሀሴ 1 እስከ 7 ድረስ ዓለም ዓቀፍ የጡት ማጥባት ሳምንት እየተከበረ ይገኛል፡፡

የእናት ጡት ወተት መተክያ የሌለው ንጹህ እና ተስማሚ የህጻናት ምግብ ነው፡፡
እስካሁን በተጠኑት ጥናቶች መሰረት የእናት ጡት ወተት መተኪያ የሌለው ንፁህ እና ተስማሚ የህፃናት ምግብ ነው፡፡

ህፃናት ያለምንም ተጨማሪ ምግብ የመጀመሪያዎቹን 6 ወራት የእናት ጡት ወተት ብቻ ማግኘት አለባቸው፡፡

ጡት ማጥባት ለእናትም ለልጅም የራሱ ጥቅም አለዉ፡፡

የእናት ጡት ወተት ማጥባት ለእናቶች ያለው ጥቅም
ከወሊድ በኋላ የደም መፍሰስ እንዳይከሰት ይከላከላል፡፡
ከወሊድ በኋላ ክብደትን ለመቀነስ ይረዳል::

የጡት እና የእንቁላል ማምረቻ ካንሰርን ይከላከላል
በእድሜ የሚመጡ በሽታዎችን ለምሳሌ ስኳር፣ ግፊት ፣የልብ ህመም እና የመሳሰሉትን በሽታዎችን ይከላከላል
በእናት እና በልጅ መሃል ያለውን ፍቅር ይጨምራል
ከወሊድ በኋላ የሚመጣውን ጭንቀት ይቀንሳል
እናት ስታጠባ ከአዕምሮዋ የሚመነጨው (ኦክሲቶሲን)የሚባል ሆርሞን ደስተኛ እንድትሆን እና ተጨማሪ ወተት እንድታመርት ያደርጋል
በተፈጥሮ ፀጋ የሚገኝ ስለሆነም ወጪ ቆጣቢ ነው ::
ለአጭር ጊዜ ቢሆንም እርግዝናን ይከላከላል(እስከ 6 ወር ወይንም የወር አበባ እሰኪመጣ)

የእናት ጡት ወተት ለህጻናት ያለው ጥቅም
ትክክለኛ እና በቂ የሆኑ ንጥረ ነገሮች በውስጡ ስለያዘ ህፃናት በተገቢው ሁኔታ እንዲያድጉ እና ብሩህ አዕምሮ እንዲኖራቸው ይረዳል፡፡
የተለያዩ ኢንፌክሽኖችን ይከላከላል፡፡

ህፃናትን ከተቅማጥ እና ተያያዥ በሽታዎች ይከላከላል፡፡
ልጆች ከመጠን ያለፈ ውፍረት እንዳይኖራቸዉ ይረዳል፡፡
የመጀመርያዉ አይነት የስኳር በሽታንም ይከላከላል፡፡
ድንገተኛ የሆነ የጨቅላ ህፃናትን ሞት ይከላከላል፡፡

የእናት ጡት ወተት ማጥባት ለቤተሰብ ፣ለማህበረሰብ እና ለሀገር ያለው ጥቅም
ወጪ ቆጣቢ እና በተፈጥሮ የተሰጠ ነው
የተለያዩ የህፃናት በሽታ በመከላከል የሀገሪቱን የጤና ወጪ ይቀንሳል
በአጠቃላይ የህፃናትን በሽታዎች በመቀነስ በሀገር ደረጃ የህፃናት ሞትን በእጅጉ ይቀንሳል
ልጆች ባለ ብሩህ አዕምሮ ሆነው እንዲያድጉ በመርዳት በትምህርትም ዉጤታማ እንዲሆኑ ከዛም እንደ ሀገር ጥሩ አበርክቶ እንዲኖራቸዉ ቀላል የማይባል አስተዋፆ አለው::

የሚያጠቡ እናቶች ማወቅ ያለባቸው ነገሮች
ህፃናት ገና በተወለዱ በ 1 ሰአት ዉስጥ ጡት መጥባት መጀመር አለባቸው፡፡
ከዛ ጀምሮ በ24 ሰአት ዉስጥ ቢያንስ ከ8 እስከ 12 ጊዜ ጡት መጥባት አለባቸው፡፡ በተጨማሪም ሕፃኑ ለመጥባት በሚፈልግበት ጊዜ ሁሉ ማጥባት ተገቢ ነው::

ህፃናት ጡት ለመጥባት ሲፈልጉ የሚያሳዩት ምልክቶች
እጃቸውን መጥባት
በደንብ ነቅተው አፋቸውን ማንቀሳቀስ
ምላሳቸውን ወጣ ወጣ ማድረግ
መነጫነጭ
ማልቀስ ናቸዉ፡፡

መረጃዉን ከቅዱስ ጳዉሎስ ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ አግኝተናል፡፡

በእስከዳር ግርማ

ሐምሌ 30 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *