አትሌት ብርቄ ሀየሎም የማጣርያ ውድድሯን ዳግም አድርጋ አንደኛ ደረጃን በመያዝ ለግማሽ ፍፃሜ ማለፏን አረጋግጣለች።ብርቄ ሀይሎም በአሁኑ ውድድሩ የግሏን ምርጥ ሰዓት አስመዝግባለች።
አትሌት ብርቄ ሀየሎም በአዲሱ የ “ repechage “ህግ መሰረት ውድድሯን ዳግም አድርጋ ነው ማለፍ የቻለችው።
የግማሽ ፍፃሜ ውድድር ነገ ከምሽቱ 2፡45 ጀምሮ ይደረጋል።
አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ እና ድርቤ ወልተጂ ለግማሽ ፍፃሜው ያለፉ ሌሎች አትሌቶቻችን ናቸው።
በ 5000 ሜ ወንዶች ማጣሪያ ውድድር በመጀመሪያው ምድብ የተሳተፈው ኢትዮጵያዊው አትሌት ሀጎስ ገብረ ህይወት በሁለተኛ ሆኖ ውድድሩን በማጠናቀቅ ለፍፃሜ ማለፉን አረጋግጧል።
በሁለተኛው ምድብ ማጣሪያ የተካፈሉት ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ቢኒያም መሀሪ እና አዲሱ ይሁኔ ለፍፃሜ ማለፋቸውን አረጋግጧል።
ምሽት 4:40 :- 3000ሜ ወንዶች መሰናክል ፍፃሜ
አትሌት ለሜቻ ግርማ
አትሌት ጌትነት ዋሌ
አትሌት ሳሙኤል ፍሬው
በጋዲሳ መገርሳ
ነሃሴ 1 ቀን 2016 ዓ.ም
