“በአሁናዊ የኢትዮጵያ ወቅታዊ ችግር ላይ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ማድረግ ኢኮኖሚያዊ ቀውሶችን ያስከትላል” አለ የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ፓርቲ/ኢሕአፓ/

የኢሕአፓ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንት መጋቢ ብሉይ አብርሃም ሃይማኖት ያቀረቡት የፓርቲው መግለጫ መንግሥት የወሰደው እርምጃ በርከት ያሉ ችግሮች ያሉበት በመሆኑ መንግሥት “ብድርን በሌሌች አማራጮች” እንዲተካ ጠይቋል፡፡

ኢሕአፓ መንግሥት የፖሊሲ ለውጥ ውሳኔውን እንዲሰርዝ ባወጣው መግለጫ አሳስቧል፡፡

“የብር ዋጋ ቅናሽ ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን ውድ ስለሚያደርገው አጠቃላይ የዋጋ ንረትን ያስከትላል፣ የብር ዋጋ ማሽቆልቆል የመግዛት አቅምን ስለሚሸረሽር ለነዋሪዎች ከፍተኛ የኑሮ ውድነት ያስከትላል፣ የኢንቨስተሮችን እምነት ሊያዳክም ስለሚቸል የካፒታልን ወደ ውጭ መፍለስንና ያስከትላል፣ የሀገሪቱን የመከፈል አቅም ይቀንሳል፤ የዕዳ ቀወስ ሊያስከትል ይችላል”

የሰዎችን ተዘዋውሮ የመሥራት መብት እና የምርት ዕድገትን እንዲገደብ ያደረገውን “የጎሳ ፌዴራሊዝም” ሥርዓት ማሻሻል አለበት ብሏል ፖርቲው፡፡

ኢሕአፓ መንግሥት “በከፍተኛ ጥንቃቄ የተዘጋጀ” እና ዘላቂ ሀገራዊ ጥቅም ያለው መሆኑን በመግለጽ ተግባራዊ ማድረግ የጀመረውን ይህን የኢኮኖሚ ማሻሻያ እንዲሰርዘው ወይም እንዲያሻሽለው ጠይቋል።

የፓርቲው ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንት ውሳኔው መንግሥት በአለም አቀፍ ደረጃ ተዓማኒነቱን የማጣቱ ማሳያ ነውም ብለዋል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ነሃሴ 1 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *