በተለያዩ የድንበር ከተሞች የሚገቡ የቦንዳ ልብስ ወይም ሰልባጅ በከተማ ዉስጥ በስፋት ገበያ ላይ መዋሉ አምራቾች ከገበያ እንዲወጡ ማድረጉን የኢትዮጵያ ጨርቃጨርቅ እና አልባሳት ማህበር ገልጿል።
በ 5 አመታት ዉስጥ 1.48 ቢሊየን ብር የሚያወጡ የቦንዳ ልብሶች በጉምሩክ መያዛቸዉን የማህበሩ ዋና ፀሀፊ አጋዚአ ገ/ እግዚአብሔር ተናግረዋል።
በአመታዊ እድገቱ በአማካይ 28.3 መድረሱን የሚናገሩት ዋና ፀሀፊዉ የቦንዳ ልብሶች በሀገሪቱ እየተሰራጩ መሆኑን ለሀገር ዉስጥ አምራቹች ፈተና መሆኑን ገልፀዋል ።
ከነዚህ ገበያዎች ጋር ፍትሀዊ የሆነ የገበያ ዉድድር እና ስርአት እንዲኖር በተደጋጋሚ ለሚመለከታቸው አካላት ቅሬታዎችን ማሰማቱን ማህበሩ አስታወሷል።
ሚያዝያ ወር ላይ በወጣዉ የማህበሩ ጥናት የሀገሪቱ የጨርቃጨርቅ ኢንዱስትሪ ገበያ እነዚህ የቦንዳ አልባሳት ገበያ 53 በመቶ ድርሻ እንዳላቸዉ አመላክቷል።
በጨርቃጨርቅ ኢንዱስትሪ ዘርፍ በ 10 አመታት ዉስጥ 4.4 ቢሊየን ዶላር ኪሳራ እንደደረሰ ተጠቅሷል።
ቁምነገር አየለ
ነሃሴ 2 ቀን 2016 ዓ.ም
