ጄም-ኮርፕ ለኢትዮ ኤፍ ኤም በላከው መግለጫ 200 ሺ ሜትሪክ ቶን ስንዴ ለብሔራዊ የአደጋ መከላከል እና ዝግጁነት ኮሚሽን መሥሪያ ቤት ለማቅረብ ለተጨማሪ ዙር ጨረታውን ማሸነፉን አስታውቋል፡፡
በኢትዮጵያ የጄም-ኮርፕ ተቋም ሥራ አስኪያጅ የሆኑት ኮስታስ ላለፉት 18 ወራት ጄምኮርፕ ጠንካራ እና አስተማማኝ የግብርና ምርቶች ንግድ ሥርዓትን በኢትዮጵያ ውስጥ ለመዘርጋት በርካታ ተግባራትን ያከናወነ ሲሆን በአሁን ሰዓትም ፉርኖ ዱቄት እና የምግብ ዘይትን ለመንግሥት እና ለግል አስመጪዎች የማቅረብ ሥራን እያከናወነ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡፡
የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ በበርካታ የኢንቨስትመንት ሥራዎች እና የንግድ አማራጮች እንዲሁም ከፍተኛ የውጪ ምንዛሪ በማስገኘት ለመደገፍ እየሰራን ነው ያሉት ስራ አስኪያጁ አስፈላጊ የሆኑ ምርቶች በዘላቂነት ለሀገር ውስጥ ገበያ መቅረባቸውን ለማረጋገጥ እንሠራለንም ብለዋል፡፡
ተቋሙ የአቅርቦት እና ሥርጭት ጉዳዮች ላይ ድጋፍ የሚሰጥ የአንድ መስኮት አሠራር መዘርጋቱንም ያስታወቁት ስራ አስኪያጅ በዚህ የአንድ መስኮት አሠራርም ለመንግሥታዊም ሆነ መሰል ተቋማት ከንግድ ጋር የተያያዙ በርካታ አገልግሎቶችን ይሰጣል ብለዋል፡፡
ጄምኮርፕ ኢኮኖሚውን በንግድ ሥራ ለመደገፍ እና ኢንቨስት ለማድረግ የኢትዮጵያን ገበያ የተቀላቀለው በ2010 ዓ.ም. ሲሆን ከዚያን ጊዜ አንሥቶ 900 ሺ ቶን ፉርኖ ዱቄት እና ከ23 ሚሊየን ሊትር በላይ የምግብ ዘይት ለኢትዮጵያ የምግብ ገበያ አቅርቧል ተብሏል፡፡
ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8
በትግስት ዘላለም
ግንቦት 14 ቀን 2012 ዓ.ም
