የወረዳው የጤና ቢሮ ሃላፊ አቶ ግርማው በይኖ ከ8መቶ 50 በላይ ህፃናት አጣዳፊ የምግብ እጥረት 5ሺ 6መቶ ህጻናት ደግሞ መካከለኛ የምግብ እጥረት አጋጥሟቸዋል ብለዋል።
በዚህም የእናቶች እና ህጻናትን የምግብ እጥረት ማሻሻል አለመቻሉንም አንስተዋል።
በተጨማሪ በወረዳው የተከሰተው ከእንስሳት ወደ ሰው የሚተላለፈው አባ ሰንጋ(Anthrax) በሽታ ከ 1 መቶ 60 በላይ ሰዎች ተይዘው አራት የሚሆኑት መሞታቸውን እንዲሁም በኩፍኝ እና ትክትክ በአጠቃላይ አራት ህፃናት ህይወታቸው ማለፉን ገልጸዋል።
ለወረርሽኞቹ መባባስ ከ 2014 ዓ.ም በፊት በክልሉ አጋጥሞ ከነበረው ጦርነት ጋር በተያያዘ ክትባቶችን ተደራሽ ማድረግ ባለመቻሉና በአብዛኛው በወረዳው የሚገኙ የጤና ተቋማት የባለሞያ ስብጥር ችግር መኖር እንደምክያት እንዳሚጠቀስ አቶ ግርማው ተናግረዋል።
ለአለም አሰፋ
ነሐሴ 09 ቀን 2016 ዓ.ም
