የሊቢያው ማዕከላዊ ባንክ [ሲቢኤል] ከቤታቸው ታፍነው የተወሰዱት የባንኩ ባለሥልጣን መለቀቃቸውን ተከትሎ አቁሞ የነበረውን ሥራ መጀመሩን አስታውቋል።

ሰቢኤል እንዳለው የባንኩ ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ክፍል ኃላፊ የሆኑት ሙሳብ ሙስላም እሑድ ዕለት ነው “ባልታወቁ ሰዎች” ከመኖሪያ ቤታቸው ታፍነው የተወሰዱት።

ባንኩ እንዳለው ሙሳብ ከዋና ከተማዋ ትሪፖሊ ሲሆን ታፍነው የተወሰዱት ሌሎችም የባንኩ ሠራተኞች የእገታ ማስፈራሪያ ደርሷቸዋል።

ሲቢኤል፤ ሙሳብ እስካልተለቀቁ ድረስ በሩን ለደንበኞች እንደማይከፍት አስታውቆ ነበር።

ሰኞ ከሰዓት አጠር ያለ መግለጫ የለቀቀው ባንኩ፤ ሙሳብ “ደኅንነታቸው ተጠብቆ” በመለቀቃቸው ምክንያት ሥራ መጀመሩን ይፋ አድርጓል።

ማዕከላዊው የሊቢያ ባንክ ገለልተኛ ቢሆንም የሊቢያ መንግሥት ንብረት ነው።

ባንኩ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሊቢያን የነዳጅ ግብይት መፈፀም የሚችል ብቸኛው እውቅና ያለው ድርጅት ነው።

በነዳጅ ሀብቷ የምትታወቀው ሊቢያ ለበርካታ ዓመታት በእርስ በርስ ጦርነት እየማቀቀች ሲሆን ትሪፖሊ የሚገኘው መንግሥት እና መቀመጫውን ቤንጋዚ ያደረገው መንግሥት ለሥልጣን እየተጋደሉባት ይገኛሉ።ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ነሐሴ 14 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *