ከዘጠኝ መቶ በላይ ቤቶች በጎርፍ ተውጠዋል፡፡
በስልጤ ዞን ከ9 መቶ በላይ ቤቶች በጎርፍ መዋጣቸው ተነገረ።
እንደዚሁም በጎርፍ አደጋው ምክንያት ከ6ሺህ በላይ ዜጎች ለከፋ አደጋ እንደተጋለጡም ነው የተነገረው።
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ስልጤ ዞን በተከሰተው የጎርፍ አደጋ ሳብያ ለጉዳት የተጋለጡ ዜጎች ቁጥር እያሻቀበ እንደሚገኝ ነው የተነገረው።
የስልጤ ዞን ኮሚኒኬሽ ሃላፊ አቶ ሳሊ ሃሰን ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናሩት አሁን ላይ የጎርፉ ጉዳት በስምንት ቀበሌዎች መከሰቱን አንስተዋል።
በዚህም ከ6 ሺህ በላይ የቤተሰብ አባላት ለከፋ አደጋ መጋለጣቸውን አቶ ሳሊ ሃሰን ጠቁመዋል።
በተያዘው የክረምት ወቅት ተከታታይ ዝናብ እንደሚቀጥል የሚያሳዩ የሜትኦሮሎጂ መረጃዎች በመኖራቸው የጎርፍ ተጋላጭ አካባቢዎች ላይ ክትትል ሲደረግ እንደነበረም ገልጸዋል።
ተፈናቃዮች ባሉበት ሁኔታ ደራሽ እርዳታ ለማድረስ ምግብና ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሶች ወደ ዞኑ ማቅረብ መጀመሩን ተናግረዋል።
በሔኖክ ወ/ገብርኤል
ነሐሴ 20 ቀን 2016 ዓ.ም
