የባንኩ ከፍተኛ አመራሮች እና ሰራተኞች በተገኙበት የተካሄደው የችግኝ ተከላ መርሀ ግብር ከ 1 ሺህ በላይ ችግኞች እንደተተከሉ ተገልፆል፡፡
ህብረት ባንክ ማህበረሰብ ተኮር የሆኑ የልማት ስራዎች ላይ ትኩረት አድርጎ እንደሚሰራ እና የአርንጎዴ አሻራ መርሀግብሩም አንደኛዉ አካል መሆኑን
የባንኩ ከፍተኛ ሀላፊ የሆኑት ወ/ሮ ፅጌረዳ ተስፋዬ ገልፀዋል፡፡
በተጨማሪም ለተተከሉት ችግኞች እንክብካቤ እና ጥበቃ የማድርግ ስራን ለማርኬቲንግ ዲፓርትመን ተሰጥቶ የቁጥጥር እና የክትትል ስራ እየተሰራ መሆኑን ሀላፊዋ ገልፀዋል፡፡
በዚህ ታሪካዊ ቀን አሻራችን በማሳረፋችን ታላቅ ደስታ ይሰማናል ያሉት ደግሞ የባንኩ ሰራተኞች ናቸዉ፡፡
ማህበራዊ ሀላፊነቱን በተለያዩ ስራዎች በመሳተፍ እየተወጣ እንደሚገኝ የተገለጸው ባንኩ ወደፊትም አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቋል፡፡
በአቤል እስጢፋኖስ
ነሃሴ 20 ቀን 2016 ዓ.ም
