የጉበት ካንሰር (Liver or Hepatic Cancer)

  • በአለም ላይ በየዓመቱ ስምንት መቶ ሺህ አዳዲስ ሰዎች በጉበት ካንሰር በሽታ ይጠቃሉ፡፡
  • በአለም አቀፍ ደረጃም በገዳይነት ከፍተኛውን ደረጃ የሚይዝ ሲሆን፤ በየዓመቱም ከ 7መቶሺህ ሰዎች በላይ ህይወታቸውን በዚህ ህመም ምክንያት ያጣሉ ።
  • ስለ ጉበት ካንሰር ማብራሪያ የሰጡን በቅዱስ ጳዉሎስ ሚሌኒየም ህክምና ኮሌጅ የዉስጥ ደዌ ህክምና ክፍል ረዳት ፕሮፌሰር እና የጨጓራ ፣የአንጀት እና የጉበት ሰብ ስፔሻሊስት ሀኪም የሆኑት ዶክተር ሚፍታህ ደሊል ሀሚድ ናቸዉ።

የጉበት ካንሰር መነሻ ምክንያት ምንድን ነዉ?

  • ለጉበት ካንሰር መነሻ ሲሮስስ ወይንም ጠባሳ የምንለዉ ሲሆን ፤በተደጋጋሚ ጉበታችን በሚቆስልበትና በሚድንበት ወቅት መጨረሻ ላይ ጠባሳዉ እየበዛ ስለሚመጣ በቀላሉ ካንሰር ማብቀል ይጀምራል ፡፡
  • ጠባሳው የሚፈጠረዉ በቫይረሶች ሲሆን፤ ሄፓታይተስ ቢ እና ሄፓታይተስ ሲ ቫይረሶች ዋነኛዉን ስፍራ ይወስዳሉ፡፡
  • በኢትዮጵያ ዉስጥ በተደረገ ጥናት 54 በመቶ የሚሆነው የጉበት ካንሰር ህመም መነሻዉ ሄፓታይተስ ቢ ቫይረስ ነዉ፡፡

በጉበት ካንሰር የተጠቃ ሰዉ ምን አይነት ምልክቶችን ሊያሳይ ይችላል ?

  • የተበላሸ ጉበት መጨረሻ ደረጃ ላይ ሲደርስ የሚያሳየው ምልክት ሆድ መንፋት፣ማበጥ እና ጉበታችን ዉሀ መያዝ ነዉ፡፡ በዚህም እብጠት ይፈጠራል፡፡
  • በተጨማሪም የደም ማስመለስ ይኖራል ምግብ ለመመገብ መቸገርም አብሮ ይመጣል፡፡
  • ክብደት የመቀነስ ምልክቶች ስለሚታዩም ይህንን ልብ ብሎ ወደ ህክምና ቦታ ቶሎ መሄድ ያስፈልጋል፡፡
  • ወደ ህክምና ተቋም በቶሎ ካልተሄደ በ6 ወራት ጊዜ ዉስጥ ህይወትን ሊነጥቅ ይችላል፡፡
  • ህመሙ አንዳንድ ጊዜ በቤተሰብ የመተላለፍ እድል እንዳለዉ ያነሱት ባለሙያው ፤ሄፓታይተስ ቢ ቫይረስ ያለበት ሰዉ ካለ ግን የበለጠ ለበሽታው ተጠቂ ይሆናል ብለዋል።

ወደ ህክምና ተቋምስ መች ነዉ መሄድ ያለብን ?

  • አብዛኛዎቹ የጉበት ካንሰር (Liver cancer) ያለባቸው ህመምተኞች ምንም አይነት የበሽታ ምልክት አያሳዩም።
  • ነገር ግን የተወሰኑ አጠራጣሪ የሆኑ ምልክቶች ይኖራሉ ለምሳሌ የሆድ ህመም፣ ሆዳችን የመነፋት ስሜት፣ ድካም፣ የምግብ ፍላጎት መቀነስ፣ የሰውነት ክብደት መቀነስ፣ የአይናችን ቀለም ቢጫ መሆንና ከበድ ያለ ደረጃ ላይ ከደረሰ ሆድ ላይ ጤናማ ያልሆነ ፈሳሽ መጠራቀም (ascites) ምልክቶችን ያሳያል።
  • ከዚህ በፊት የጉበት ህመም ታመዉ የሚያዉቁ ከሆነ በተለይም በሄፓታይተስ ቢ ወይም በሄፓታይተስ ሲ ታመዉ ከሆነ በየ6 ወራት አልትራሳዉንድ መነሳት ያስፈልጋል፡፡
  • በተደጋጋሚ በሚከሰት የጉበት ህመም ምክንያት ደግሞ ሲሮሲስ ወይም ጠባሳ ካለም በየስድስት ወሩ እብጠቶች መኖራቸዉን ለማረጋገጥ አልትራ ሳዉንድ መነሳት የሚያስፈልግ መሆኑን ባለሙያዉ ገልጸዋል፡፡

በሊዲያ ደሳለኝ

ነሐሴ 20 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *