በአዲስ አበባ ከተማ ሀያት ጸበል ለሚገነባው ህንፃ 1.7 ቢሊዮን ብር እንደሚያስፈልግ መቄዶኒያ የአረጋዊያንና የአእምሮ ህሙማን ማዕከል አስታውቋል።
ለሚገነባው ህንፃ ማጠናቀቂያ የሚሆን የገንዘብ ማሰባሰብ መርኅ ግብር ከዚህ ቀደም መከናወኑን ያስታወሱት እና ሙሉ በሙሉ የህንፃውን ግንባታ ለማጠናቀቅ 1.7 ቢሊዮን ብር ያስፈልጋል የተናገሩት የማዕከሉ መስራች ቢኒያም በለጠ ናቸው።
በማዕከሉ 7 ሺህ 5 መቶ የሚሆኑ ዜጎች እንደሚገኙ የተገለፀ ሲሆን፤ በግንባታ ላይ የሚገኘው ባለ15 ወለል ህንፃ ለማጠናቀቅ በሂደት ላይ መሆኑ ተገልጿል።
የሚገነባው ህንፃ ሲጠናቀቅ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎችን ከጎዳና ላይ ለማንሳት እና ለመርዳት እንደሚቻል ተነግሯል።
በእሌኒ ግዛቸው
ነሐሴ 20 ቀን 2016 ዓ.ም
