ዳሸን ባንክ ከኤግል ላየን ቴክኖሎጂ ጋር በመተባበር “ካሽ ጎ” (CashGo) የተሰኘ ዓለም ዓቀፍ የሃዋላ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል፡፡
“ካሽ ጎ” በቀላሉ በሞባይል መተግበሪያ የሚሰጥ አገልግሎት ሲሆን ተጠቃሚዎች በተለያዩ የዓለም ሀገራት የሚገኙ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የእጅ ስልካቸውን ብቻ በመጠቀም ለወዳጅ ዘመዶቻቸው በቀላሉ ገንዘብ መላክ የሚችሉበት ቴክኖሎጂ ነው፡፡
ከውጭ ሃገር ወደ ኢትዮጵያ በዳሸን ባንክ “ካሽ ጎ” በኩል ከነሐሴ 27 እስከ መስከረም 20/2017 ዓ.ም ድረስ የተላከን ገንዘብ ለሚቀበሉ ደንበኞች ከዕለታዊ ምንዛሬው ተመን ተጨማሪ የ15 በመቶ ጉርሻ (ቦነስ) ያገኛሉ፡፡
አገልግሎቱ የውጭ ምንዛሬ የማግኘት አቅምን በእጅጉ ከማሳደጉም በተጨማሪ ገንዘብ ወደ ሀገር ውስጥ መላክ ለሚያስብ ማንኛውም ከሀገር ውጪ የሚኖር ሰው ከሌሎች የሀዋላ መላኪያ ዘዴዎች ወዲያዉኑ ገንዘብ መላክ የሚያስችል ነው፡፡
“ካሽ ጎ” ገንዘብ ወደ ሀገር ቤት ለመላክ ለሚያስብ ሰው ከሌሎች የሀዋላ መተግበሪያዎች ገንዘብ ላኪም ሆነ ተቀባይ ያለምንም ክፍያ ገንዘባቸውን መላክ የሚችሉበት መንገድ ነው፡፡
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ነሐሴ 27 ቀን 2016 ዓ.ም
