በቀጣዮቹ 10 ቀናት በአንዳንድ ቦታዎች ላይ ከፍተኛ የሆነ የዝናብ መጠን ስለሚኖር የጎርፍ ተጋላጭ በሆኑ አካባቢዎች ላይ ጥንቃቄ መደረግ እንዳለበት የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት አሳሰበ፡፡

በመደበኛ ሁኔታ በቀጣዮቹ 10 ቀናት የክረምቱ ዝናብ በስርጭትም ሆነ በመጠን ከምሥራቅ አጋማሽ የሀገሪቱ ክፍሎች ቀስ በቀስ የመቀነስ አዝማሚያ እንደሚያሳይ ኢንስቲትዩቱ ገልጿል::

በአንጻሩ በመካካለኛው፣ በምዕራብ፣ በደቡብ ምዕራብ እንዲሁም በሰሜን ምዕራብ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ ጠንካራ እና የተስፋፋ የዝናብ መጠንና ስርጭት እንደሚኖር ተጠቅሷል፡፡

በተጨማሪም በመካከለኛው፣ በሰሜን ምዕራብ፣ በምዕራብ እና በደቡብ ምዕራብ የሀገሪቱ አካባቢዎች በ24 ሠዓት ውስጥ ከ30 ሚሊ ሜትር በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚኖር ተጠቁሟል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ነሐሴ 27 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *